ስለ ጻድቅ ተብሎ መቆጠር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጻድቅ ተብሎ መቆጠር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ነገር ግን ለማይሠራ ይልቁንም ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ለእርሱ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
ቅዱሱ መጽሐፍ ምን ይላል? "አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፥ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" ይላል።
አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።
ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት»
ስለዚህ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ተቆጠረለት የባለው ለእርሱ ጥቅም ብቻ የተጻፈ አይደለም። ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም ደግሞ ይቆጠርልን ዘንድ ተጽፏል።
እንግዲህ ይህ በረከት የተነገረው በተገረዙት ላይ ብቻ ነው ወይስ ደግሞ ባልተገረዙትም ላይ? "ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" እንላለን።
ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን በሚቆጥርለት ሰው ላይ በረከትን ይናገራል።
ያህዌ በደሉን የማይቆጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ቡሩክ ነው፡፡
“አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ። ስለዚህም አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።
አብርሃም የመገረዝን ምልክት ተቀበለ። ይህም ከመገረዙ በፊት አስቀድሞ በእምነት ላገኘው ጽድቅ ማኅተም ነበር። የዚህ ምልክት ውጤት ምንም እንኳን ባይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት መሆኑ ነው። ይኸውም ጽድቅ ይቆጠርላቸዋል ማለት ነው።
እንግዲህ በሕግ ላይ የተመሠረተው የራሴ ጽድቅ የለኝም። በዚህ ፈንታ በክርስቶስ በኩል በሚገኝ እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ አለኝ።
እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።