ስለ የእግዚአብሔር ጽድቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ፊልጵስዩስ 3:9

እንግዲህ በሕግ ላይ የተመሠረተው የራሴ ጽድቅ የለኝም። በዚህ ፈንታ በክርስቶስ በኩል በሚገኝ እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ አለኝ።

02 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21

እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።

03 ሮሜ 3:21-22

አሁን ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጧል። ልዩነት ሳይደረግ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ ይሆንላቸው ዘንድ በሕግና በነቢያት የተመሰከረ ነው።

04 ሮሜ 1:17

"ጻድቅ በእምነት ይኖራል" ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ በወንጌል ከእምነት ወደ እምነት ተገልጧልና።

05 ኤርሚያስ 23:6

በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፣ እስራኤልም በአስተማማኝ ደህንነት ይቀመጣል። የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ተብሎ ነው።

06 ሮሜ 3:26

አቀረበው። በዚህ በአሁኑ ዘመን የእርሱ ጽድቅ እንዲታይ ይህ ሁሉ ሆነ። እንዲህም የሆነው እርሱ ጻድቅ መሆኑንና በኢየሱስ የሚያምነውን ሁሉ የሚያጸድቅ ራሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።

07 ሮሜ 10:3-4

የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁምና የራሳቸውን ጽድቅ ሊመሰርቱ ይጥራሉ፤ለእግዚአብሔርም ጽድቅ ራሳቸውን አያስገዙም። ምክንያቱም ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ ለጽድቅ የሚሆን የህግ ፍጻሜ ነው።

08 ኢሳይያስ 61:10

አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፣ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፣ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፣ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፣ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።

ተዛማጅ ርዕሶች