ስለ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።
በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።
ይህም በፀጋው ፀደቅን፣ የዘላለም ህይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን ነው።
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።
ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን
እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።
ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።
በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።
ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።
ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም። ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል።
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ እንዴት ሁሉን ነገር ደግሞ ከልጁ ጋር በነጻ አይሰጠንም?
ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።
የተወደዳችሁ ወንድሞች ስሙ፤ በእምነት ባለ ጸጋ እንዲሆኑና፣ እርሱን ለሚወዱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት እንዲወርሱ እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ድኾችን አልመረጠምን?
ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት አብረው ወራሾች፥ አብረው የካሉ ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ በተገኘው ተስፋ አብረው ተካፋዮች መሆናቸው ነው።