ስለ የእግዚአብሔር ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር ልጆች የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 1:12

ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡

02 1ኛ ዬሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።

03 ሮሜ 8:16

የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።

04 ገላቲያ 3:26

ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።

05 ሮሜ 8:14

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።

06 1ኛ ዬሐንስ 3:2

የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።

07 ፊልጵስዩስ 2:15

ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።

08 ዮሐንስ 11:52

ደግሞም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በልዩ ልዩ ስፍራ የተበታተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ይሰበስብ ዘንድ መሞት እንደሚገባው ትንቢት ተናገረ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች