ስለ ንጹሕ ሕሊና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ንጹሕ ሕሊና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ነገር ግን የትእዛዙ ግብ ከንጹህ ልብ፣ ከመልካም ኅሊና እና ከእውነተኛ እምነት የሚወጣ ፍቅር ነ
በዚህም በሁሉም ነገር በእግዚአብሕርና በሰዎች ፊት ነቀፋ የሌለበት ኅሊና እንዲኖረኝ እሠራለሁ።
በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
በሁሉም ነገር የከበረ ሕይወት ለመኖር የሚፈልግ ንጹሕ ኅሊና ስላለን ጸልዩልን።
ስለዚህም እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ክደው መርከብ አለመሪ እንደሚጠፋ በእምነት ነገር ጠፍተዋል፡፡
ሌትና ቀን በጸሎቴ ስለማስብህ፣ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹህ ኅሊና የማገለግለወን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣
በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም፣ ህሊናዬ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ይመሰክርልኛል፣
የምንመካው በህሊናችን ምስክርነት ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንመላለስ የነበረው በንፁህ ህሊና እና ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ቅንነት ነበር። በተለይም ከናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ እንጂ በምድራዊ ጥበብ ላይ አልነበረም።
ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?
ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።
ጳውሎስም ትኵር አድርጎ ወደ ሸንጎው በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ እስካሁን ድረስ፣ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ኅሊና ሁሉ ኖሬአለሁ” አለ።
ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤
ስለዚህ ስለ ቁጣው ብለህ ብቻ ሳይሆን ስለህሊናህ ብለህ ልትገዛ ይገባሀል።
ንጹሆች ለሆኑት፣ ሁሉም ንጹህ ነው፣ ለርኩሶችና ለማያምኑ ግን ንጹህ የሆነ ምንም የለም። ይልቁን፣ አዕምሯቸውና ሃሳባቸው እንኳ የረከሰ ነው፡፡
ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን።