ስለ የቃሉ ዘር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የቃሉ ዘር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ትርጕም እንደዚህ ነው፣ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ነገር ግን በመልካሙ ዐፈር ላይ የወደቁት በመልካምና በቅን ልብ ካደመጡ በኋላ ቃሉን አጥብቀው የሚይዙ በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
መሬት የወደቁት እነዚህ ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት ናቸው ሰላሳ እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው፡፡
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።
በመልካም መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማና የሚረዳ ነው፤ በርግጥ የሚያድገውና ፍሬ የሚሰጠውም ይህኛው ነው፤ አንዱ መቶ፣ አንዱም ሥልሳ፣ አንዱም ሠላሣ እጥፍ ያፈራል።
ዘሪው ቃሉን ዘራ፡፡
ከዘሩ አንዳንዱ ግን በመልካም ዐፈር ላይ ወደቀ መቶ እጥፍ ፍሬም አፈራ።" ኢየሱስ ይህንን ከተናገረ በኋላ ጮኽ ብሎ፣ "ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።
ከዚያም ኢየሱስ በምሳሌ ብዙ ነገር ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ "ዘሪ ለመዘራት ወጣ። ሲዘራም፣ አንዳንዱ ዘር በመንገድ አጠገብ ወድቆ፣ ወፎች መጥተው በሉት። ሌላውም ዘር በቂ አፈር በሌለበት በዐለታማ መሬት ላይ ወደቀ። አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ። ፀሐይ ሲወጣ ግን፣ሥር ስላልነበረው ጠውልጎ ደረቀ። ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፣ እሾኹም አድጎ አነቀው። ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ አፈራ፤ አንዳንዱ መቶ፣ አንዳንዱ ሥልሳ፣ አንዳንዱም ሠላሳ ፍሬ አፈራ። ጆሮ ያለው ይሰማ።"
ስለዚህ ርኵሰትንና በየቦታው ሞልቶ ያለውን ክፋት አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁ የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ ምድርን እንደሚያረካት፣ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፣ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፣ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
አለ የእግዚአብሔር መንግሥት በመሬት ላይ ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች፡፡ ሲመሽ ይተኛል ሲነጋም ይነቃል፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላወቀው መልኩ ዘሩ አቆትቁጦ በቀለ፡፤
እኔ ተክልሁ አጽሎስም አጠጣ፤ ግን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው።
“አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ።እንደ ዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ተረገጠ፣ የሰማይ ወፎችም መጥተው በሉት።
እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ዘር ወደ ምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡
አትታለሉ እግዚአብሔር አይቀለድበትም።ሰው ምንም ነገር ቢዘራ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል። በሥጋው የሚዘራ ከሥጋው ውድቀትን ያጭዳል፤በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል።