ስለ የክርስቶስ አሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የክርስቶስ አሳብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ቆሮንቶስ 2:16

"የጌታን አሳብ ማን አወቀው፤ ማንስ ሊያስተምረው ይችላል?" እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

02 ፊልጵስዩስ 2:5

በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤

03 ሮሜ 12:2

መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።

04 1ኛ ቆሮንቶስ 2:12

እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።

05 ቆላስይስ 2:3

የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።

06 ፊልጵስዩስ 2:6-8

እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ። የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ። እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።

07 ዮሐንስ 15:15

ከእንግዲህ አገልጋዮች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም አገልጋይ ጌታው ምን እያደረገ እንዳለ አያውቅም። ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ እንድታውቁ ስለ ነገርኋችሁ፣ ወዳጆች ብያችኋለሁ።

08 ኤፌሶን 4:23

በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ

09 ሮሜ 8:6

የሥጋ አስተሳሰብ ሞት ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ አስተሳሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

10 1ኛ ቆሮንቶስ 1:30

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።

11 ዮሐንስ 8:29

የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬንም አልተወኝም፤ እኔ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አደርጋለሁና።”

12 ዕብራዊያን 4:15

ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።

13 ፊልጵስዩስ 2:3

በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።

14 ኢሳይያስ 50:4

የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።

15 ዮሐንስ 5:30

እኔ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው በሰማሁት መሠረት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም፣ ፍርዴ ትክክል ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች