ስለ ባልንጀራህን ውደድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ባልንጀራህን ውደድ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ማርቆስ 12:31

ሁለተኛዋም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ ከእነዚህ የሚበልጥ ምንም ሌላ ትእዛዝ የለም አለው፡፡

ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡

03 ሉቃስ 10:27

እርሱም፣ "ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህ፣ በሙሉ ዐሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ" ብሎ መለሰ፡፡

04 ገላቲያ 5:14

ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል»

05 ሮሜ 13:9-10

ምክንያቱም «አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ አትመኝ» የሚሉትና ሌሎቹም ትዕዛዛት «ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ» በሚለው ትዕዛዝ ተጠቃለዋል። ፍቅር ያለው ባልንጀራውን አይጎዳም። ስለዚህ ፍቅር የህጉ ፍጻሜ ነው።

06 የማቴዎስ 22:39

ሁለተኛውም ትእዛዝ ያንኑ ይመስላል፤ 'ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡'

07 ያዕቆብ 2:8

ይሁን እንጂ፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ እንደ ተጻፈው የከበረውን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤

08 ሮሜ 15:2

መልካም ነውና እንድናንጸው እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ።

09 ሉቃስ 10:36-37

"ከእነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነለት የትኛው ይመስልሃል?" አለው። መምህሩም፣ "የራራለቱ ነው" አለ። ኢየሱስም፣ "አንተም ሂድና ይህንኑ አድርግ" አለው።

10 የማቴዎስ 7:12

ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ እናንተም ልታደርጉላቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሕጉም ነቢያቱም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች