ስለ ሕያው ውኃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሕያው ውኃ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዮሐንስ 7:38
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተናገሩት፣ በእኔ የሚያምን የሕይወት ውሃ ወንዝ ከውስጡ ይፈልቃል›› አለ፡፡
02 ዮሐንስ 4:14
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ፈጽሞ ዳግመኛ አይጠማም፤ ይልቁንም፣ እኔ የምሰጠው ውሃ፣ ከውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።»
03 ዮሐንስ 4:10
ኢየሱስ፣ «የእግዚአብሔርን ስጦታና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን እንደሆነ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም ሕያው ውሃ በሰጠሽ ነበር» ብሎ መለሰላት።
04 ኢሳይያስ 44:3
በተጠማ ላይ ውኃን፣ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፣ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥
መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።
06 ዮሐንስ 7:37
በታላቁ የበዓሉ ቀን፣ በመጨረሻው ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ፣ ‹‹የተጠማ ማንም ቢኖር፣ ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፡፡
07 ኤርሚያስ 2:13
ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች በእኔ ላይ አድርገዋልና፦ ውሃ ለመያዝ የማይችሉትን የተቀደዱ ጉድጓዶች ለራሳቸው በመቆፈር እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል!
ዋላ የምንጭ ውሃ እንደሚናፍቅ አምላኬ ሆይ፣ እኔም እግዚአብሔርን ተጠማሁ፡፡