ስለ በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ቆሮንቶስ 3:16

እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?

02 1ኛ ቆሮንቶስ 6:19

ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?

03 ሮሜ 8:9

ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ውስጥ መኖሩ እውነት ከሆነ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ማንም ቢሆን ይህ የእርሱ ወገን አይደለም።

04 2 ጢሞቴዎስ 1:14

በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አድርገህ በእግዚአበሔር የተሰጠህንም አደራ ጠብቅ፡፡

05 1ኛ ዬሐንስ 4:13

መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን።

06 ሕዝቅኤል 36:27

መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም መሄድ አስችላችኋለሁ ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።

07 ገላቲያ 4:6

ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።

ተዛማጅ ርዕሶች