ስለ የእውነት መንፈስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የእውነት መንፈስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዮሐንስ 16:13
ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ ነገር ግን ከእኔ የሰማውን ሁሉ እነዚያን ይናገራል፤ ደግሞም ሊመጡ ስላሉ ነገሮች ይነግራችኋል፡፡
02 ዮሐንስ 14:17
እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።
03 ዮሐንስ 14:26
የሆነ ሆኖ፣ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያስችላችኋል።
04 ዮሐንስ 15:26
ከአብ የምልክላችሁ አጽናኝ፣ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ስለ እኔ ይመሰክራል።
05 1ኛ ዬሐንስ 4:6
እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡
እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።
07 ዮሐንስ 16:14
የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ስለሚነግራችሁም ያከብረኛል፡፡