ስለ የቃሉ አድራጊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የቃሉ አድራጊዎች የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ።
ስለዚህ፣ ቃሎቼን የሚሰማና የሚታዘዛቸው ልክ ቤቱን በድንጋይ ላይ የመሠረተ አስተዋይ ሰውን ይመስላል፡፡
እርሱ ግን፣ “የተባረኩትስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው” አለ።
እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው የተባረካችሁ ናችሁ።
በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕጉን የሚሰሙት ሳይሆኑ ሕጉን የሚያደርጉት ናቸው።
ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።
በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡
ስለዚህ ሕዝቤ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት መጥተው በፊትህ ይቀመጣና ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። ትክክለኛው ቃል በፍቸው ነው ፥ ልባቸው ግን ቅንነት የሌለበትን ትርፍ ትከተላለች።
የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።
እግዚአብሔር እንደሚውያቁ ይናገራሉ፣ በሥራቸው ግን ይክዱታል። የሚያስጸይፉ የማይታዘዙና፣ ለመልካም ስራም የማይበቁ ናቸው፡፡