ስለ አክሊላት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ አክሊላት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
የጽድቅም አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ፣ የሆነው ጌታ፣ በዚያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ለእኔ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ነው፡፡
የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።
በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።
በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።
በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ። ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።