ስለ የልጁን መልክ መምሰል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የልጁን መልክ መምሰል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 8:29

ምክንያቱም አስቀድሞ ያወቃቸውን እነርሱን በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወሰነ።

02 2ኛ ቆሮንቶስ 3:18

እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እያየን እርሱን ወደሚመስል ከአንድ ክብር ደረጃ ወደ ሌላ ክብር ደረጃ እንለወጣለን፤ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነው ጌታ ነው።

03 1ኛ ዬሐንስ 3:2

የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።

04 ፊልጵስዩስ 3:21

እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል። ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኃይል ነው።

05 ገላቲያ 4:19

ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል!

06 ቆላስይስ 3:10

የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።

07 ኤፌሶን 4:24

እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

08 1ኛ ቆሮንቶስ 15:49

ልክ እኛ ከአፈር የተሠራውን ሰው እንደምንመስል፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩን ሰው መልክ እንይዛለን።

09 ሮሜ 8:28-29

እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ በዓላማው ለተጠሩት ለእነርሱ ሁሉን ነገር አጣጥሞ ለመልካም እንደሚሠራላቸው እናውቃለን። ምክንያቱም አስቀድሞ ያወቃቸውን እነርሱን በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወሰነ።

10 1ኛ ጴጥሮስ 1:15-16

ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።

11 2ኛ ጴጥሮስ 1:4

በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ የከበረና ታላቅ ተስፋ ሰጠን፤ ይህንም ያደረገው በክፉ ምኞቶች ሰበብ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።

12 ገላቲያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።

ተዛማጅ ርዕሶች