ስለ የማያሳፍር ተስፋ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የማያሳፍር ተስፋ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ልባችን ውስጥ ስለፈሰሰ ይህ ተስፋ ሐዘን የለበትም።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን በመከራዎቻችን ደግሞ ደስ ይለናል። መከራ መጽናትን እንደሚያደርግ እናውቃለን። መጽናት ተቀባይነትን፥ ተቀባይነትም ስለ ወደፊቱ መተማመኛን ያስገኛል።
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ ከቶ አያፍሩም፤ እንዲያው ያለ ምክንያት የሚያታልሉ ግን ያፍራሉ፡፡
ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።"
ምክንያቱም መጽሀፍ እንደሚል «በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ።
የዳንነው በዚህ ተስፋ ነው። ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው የማይታየውን ነው፥የሚያየውንማ ማን በተስፋ ይጠባበቃል? ገና ያላየነውን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን እንግዲያው በትዕግስት እንጠባበቀዋለን።
እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
ወደ አንተ ጮኹ፤ እነርሱም ዳኑ በአንተ ተማመኑ፤ እነርሱም አላፈሩም፡፡
ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይችልባቸው ሁለት የማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን መተማመኛ አጥብቀን ይዘን አምባ ፍለጋ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ነው። ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ቅድስት የሚገባውና እኛ የያዝነው ይህ መተማመኛ፣ ሥጋት የሌለበትና አስተማማኝ የነፍሶቻችን መልሕቅ ነው።
በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው «እነሆ፤ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም» ።