ስለ የደኅንነት እርግጠኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የደኅንነት እርግጠኝነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 1ኛ ዬሐንስ 5:13
በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።
02 ዮሐንስ 10:28
የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።
03 ሮሜ 8:38-39
ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።
04 ዮሐንስ 5:24
እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።
05 ፊልጵስዩስ 1:6
ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።