ስለ እግዚአብሔርን መፍራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ እግዚአብሔርን መፍራት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ምድር ሁሉ ያህዌን ትፍራው በዓለም ያሉ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ፡፡

ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡

03 ዕንባቆም 2:20

ያህዌ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል!»

እርሱ በቅዱሳኑ ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤ በዙሪያው ካሉትም ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው፡፡

05 ዕብራዊያን 12:28

ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣

ተዛማጅ ርዕሶች