ስለ የእግዚአብሔር ቅድስና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የእግዚአብሔር ቅድስና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።
ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።
“ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡
ጌታ ሆይ አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ የጽድቅ ስራህ ስለተገለጠ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።»
አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም።
ዐይኖችህ እጅግ የነጹ በመሆናቸው ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ዝም ብለህ አታይም፤ ታዲያ፣ እነዚያን ዐመፀኞች ለምን ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ዐመፀኛው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሰው ሲውጠውስ ለምን ዝም ትላለህ?
አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፣ "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።