ስለ የተጠበቀ ርስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የተጠበቀ ርስት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ጴጥሮስ 1:4

ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።

02 ቆላስይስ 1:12

በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።

03 ኤፌሶን 1:14

ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።

04 1ኛ ጴጥሮስ 1:5

እናንተም በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኅይል ተጠብቃችኋል።

05 ሮሜ 8:17

ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።

አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፣ እንዲሁም በቅዱሳን ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።

07 ኤፌሶን 1:18

የምጸልየውም የመጠራታችን አስተማማኝነት እና በእርሱ ቅዱሳን መካከል የርስቱ ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ

08 ዕብራዊያን 9:15

ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።

09 ገላቲያ 3:29

እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።

10 1ኛ ቆሮንቶስ 2:9

ነገር ግን፦ "ዓይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማውን፤ በሰውም ልብ ያልታሰበውን፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን ነገር" ተብሎ ተጽፎአልና።

11 የማቴዎስ 25:34

ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።

ተዛማጅ ርዕሶች