ስለ በክርስቶስ ፍጹም መሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በክርስቶስ ፍጹም መሆን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ቆላስይስ 2:10

በእርሱም ተሞልታችኋል። እርሱ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ ነው።

02 ቆላስይስ 2:9

የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት በእርሱ ይኖራልና።

03 2ኛ ጴጥሮስ 1:3

በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እግዚአብሔርን በማወቅ እንድንኖር ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ በመለኮቱ ኀይል ተሰጥቶናል።

04 ኤፌሶን 3:19

እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ፥ ከሰው ዕውቀት ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።

05 ዕብራዊያን 10:14

ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።

06 ቆላስይስ 1:28

የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።

07 ፊልጵስዩስ 1:6

ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።

08 1ኛ ቆሮንቶስ 1:30

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።

09 ኤፌሶን 1:3

በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ።

10 ዕብራዊያን 12:2

በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።

11 ፊልጵስዩስ 4:19

ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።

12 ቆላስይስ 2:6-7

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። በእርሱም ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ፤ እንደ ተማራችሁትም በእምነት ተደላድላችሁ ኑሩ፤ ምስጋናም ይብዛላችሁ።

13 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21

እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።

14 1 ተሰሎንቄ 5:23-24

የሰላም አምላክ ራሱ ፈጽሞ ይቀድሳችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ መላው መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ያለ ነቀፋ ይጠበቅ። የጠራችሁ ታማኝ ነው፣ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።

ተዛማጅ ርዕሶች