ስለ ፍሬ ማፍራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ፍሬ ማፍራት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 15:8

ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።

02 ዮሐንስ 15:5

እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ የምኖርበት ያ ሰው ብዙ ፍሬ ያፈራል። ያለ እኔ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉም።

03 ዮሐንስ 15:16

እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ነገር ግን እኔ መረጥኋችሁ፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ ሾምኋችሁ። ይህም አብን በስሜ የምትለምኑትን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጣችሁ ነው።

04 ገላቲያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።

05 የማቴዎስ 7:17

እንደዚያው፥ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል።

06 ዮሐንስ 15:2

እርሱም በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ ያማያፈራውን ማንኛውንም ቅርንጫፍ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ግን ይበልጥ ያፈራ ዘንድ ያጠራዋል።

07 ቆላስይስ 1:10

ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።

08 ፊልጵስዩስ 1:11

ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።

09 ሮሜ 7:4

ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥እናንተም በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ምውት ተደርጋችኋል። ይኸውም ለእግዚአብሔር ፍሬ እናፈራ ዘንድ ከሌላው ማለትም ከሙታን ከተነሣው ጋር እንድትተባበሩ ነው።

እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች