ስለ የሚበላ እሳት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የሚበላ እሳት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 12:29

ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው።

02 ኦሪት ዘዳግም 4:24

እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።

03 ዘጸአት 24:17

የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር።

እርሱ የሚመጠበትን ቀን ማን መቋቋም ይችላል? እርሱ ሲገለጥ ማን ፊቱ መቆም ይችላል? ምክናቱም እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ለብስ አጠቢ ሳሙና ነው።

05 ኢሳይያስ 33:14

በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፣ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?

06 ኦሪት ዘዳግም 9:3

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊታችሁ ስለሚያልፍ፥ ዛሬ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊታችሁም ያዋርዳቸዋል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገራችሁ እናንተ ታሳድዳቸዋላችሁ ፈጥናችሁም ታጠፋቸዋላችሁ።

07 ዕብራዊያን 10:31

በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው!

08 2ኛ ተሰሎንቄ 1:7-8

ጌታችን ኢየሱስ ከኀይሉ መላዕክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበላችሁት ደግሞ እረፍትን ይሰጣችኋል። እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ግን በሚነድ እሳት ይበቀላቸዋል።

09 ትንቢተ ናሆም 1:6

በቁጣው ፊት ማን መቆም ይችላል? ጽኑ ቁጣውንስ ማን መቋቋም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሶአል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጠቁ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች